GPTC Board Meeting
ቀን 24 /04 / 2018 ዓ/ም
የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትም/ስልጠና ቦርድ በክህሎት መር ስራ እድል ፈጠራ፣ በአዲሱ የዘርፉ ኢኒሸቲቦች፣ የኮሌጅን አቅም በሚያጠናክሩ የውስጥ ገቢ ማመንጫ የኢንተር ፕራይዝ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጠይ ኮሌጁን በመደገፍ ያለበትን የመሠረተ ልማት ችግሮች ለመፍታት አቅጣጫ ተቀመጠ ።
የቦርድ ስብሳቢዎ ክብርት ወ/ሮ ደብሬ የኋላ ኮሌጅ በከተማችን እና ለቀጠናው ፋይዳው ከፍ ያለ በመሆኑ የተሟላ ድጋፍ በማድረግ በዘርፉ የክህሎት ልማት የተጣለበትን ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ። በተጨማሪም በቀጣይም ከከተማ አስተዳደሩ ሰፋፊ ስራዎችን እየወሰደ የውስጥ አቅሙን የሚያጠናክር ይሆናል ብለዋል ።
ኮሌጁ በ2017 ዓ/ም የተሻለ አፈፃፀም በማምጣት በክልል ደረጀ እውቅና የተሰጠው እና በኢትዮጵያ ተሰማሚነት ምዘና ድርጅት በISO 21001:2018 EOMS ሰርቲፋይድ የሆነ ተቋም ሲሆን በቀጣይ ይህን ውጤት ማስቀጠል እንዳለበት የቦርድ አባላት አሳስበዋል ።
ጎፓቴኮ !