ISO 21001:2018 EOMS
ለጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ፣ ለጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ለአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ እንኳን ደስ ያላችሁ !!
ኮሌጅ የISO 21001:2018 EOMS አለም አቀፍ የትምህርት ጥራት ስታንዳርድ ሰርቲፋይ መሆን ችሏል።
ኢተምድ ለስድስት ድርጅቶች የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬቶችን ሰጠ።
ነሃሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
___________________________________________________________________________________________
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በትምህርት ስራ አመራር ስርዓት (ISO 21001) ሰርተፊኬቶች ሰጥቷል። ኮሌጁ በሥራ አመራር ሥርዓቶች ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን መሟላታቸውን በተከናወነላቸው የኦዲት ሂደት ተገምግሞ የተሰጣቸው ሲሆን ሰርተፍኬቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለድርጅቶቹ የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል፡፡
በሰርተፍኬቱ ርክክብ ወቅት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ በቅድሚያ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት በማስተላለፍ በዓለም አቀፍ የስራ አመራር ስርዓቶች ሰርተፍኬት ማግኘታቸው ለሚሰጡት አገልግሎት በሀገር ውስጥና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆኑ አስቻይ መሆኑን አብራርቷል። አክለውም የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዲሁም አጠቃላይ ስለ ጥራት መንደር ገለፃ በማድረግ ቀጣይ የጋራ ስራዎች ላይ ውይይት ከድርጅቶቹ የስራ ኃላፊዎች ጋር አድርገዋል፡፡