Gondar Polytechnic College / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025 #ተሞክሮ ቀጠይ በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ በ2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 30 ሰርቲፋይድ ለሚሆኑ #7 ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ አቀረበ ። በቀጣይም #የደባርቅ እና #እንጅባራ #ፖሊቴክኒክ #ኮሌጆችን ለመደገፍ በስራና ክህሎት ቢሮ በዕቅድ የተሰጠው ሲሆን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ኮሌጆችን ተረክበናል ። በመጨረሻም ጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ #ከስራና #ክህሎት #ሚኒስተር ዴታ ከክቡር #ዶር #ተሻለ #ቤረቻ በስራና ክህሎት ቢሮ በኩል #የምስጋና እና #የእውቅና #ሰርትፊኬት ተበርክቶለታል.
የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሲድ ፕሮጀክት ከሆኘ ኢንተርኘራይዝ ጋር በመተባበር ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል በሰራቸው ስራዎች የሰርትፊኬት እውቅና ተበረከተለት። የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሲድ ፕሮጀክት ከሆኘ ኢንተርኘራይዝ ጋር ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት በማድረግ ላይ ይገኛል ። ... በመሆኑም ኮሌጅ ለተከታታይ 3 ዓመት ከፕሮጀክቱ ጋር በመተባበር በርካታ ስልጠናዎችን በማሰልጠን እና የስራ ትስስር ስራዎችን በመስራቱ ሰርትፊኬት እና እውቅና ማግኘት ችሏል። በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተስፋሁን መኮነን በተገኘው እውቅና መደሰታቸውን ገልፀው ፤ ይህ አይነቱ እውቅና በቀጣይ ዓመታትም የስልጠና እና የስራ ትስስር ስራውን አጠናክረን በላቀ መንገድ ለመፈጸም ያስችላል ብለዋል።